ለ18 ዓመት በH.I.V ቫይረስ በሽታ ተይዠ
አቶ ተመቸ በላይ ይባላሉ የመጡት ከእብናት ወረዳ ሹንጌ የሳርነቁከሚባል ቀበሌ ሲሆን በወንቅ እሸት ገዳም የተደረገላቸውን ተአምር እንዲህ ሲሉ መስክረዋል፡:
እኔ ለ18 ዓመት በH.I.V ቫይረስ በሽታ ተይዠ በሀዘንና ተስፋ በመቁረጥ እኖር ነበር፡፡በተጨማሪም ለ15 ዓመት በአስም ህመም እሰቃይ ነበር፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ [read more] ከተወለድኩ 3 ዓመት ከሆነኝ ጀምሮ ለ37 ዓመት ሙሉ ከጆሮየ ደምና መግል እየፈረጠ ስሰቃይ እኖር ነበር፡፡በተለያዩ የህክምና እና የጸበል ቦታዎች ተንከራትቸ ተስፋ ከቆረጥኩ በኋላ ስለ ወንቅ እሸት ዝና ሰምቸ ወደዚህ ገዳም በመምጣት ለ4 ወር ከተጠመቅኩ በኋላ ወደ ባህር ዳር ሄጀ ጋምቢ ሆስፒታል 2 ጌዜ ተመርምሬ ከH.I.V ነጻ ነህ ተባልኩ፡፡ነገር ግን አላመንኩም፡፡እንደገናም ወደ ወረታ በመሄድ 2ጊዜ ስመረመር ከH.I.V ነጻ ነህ ተባልኩ ፡፡ በተጨማሪም እግሬን ሽባ የሚያደርግ የቁርጥማት በሽታ ነበረብኝ በወንቅ እሸት ገዳም ከH.I.V.፣ ከአስም ፣ከቁርጥማት እና ከጆሮየ ህመም ከሁሉም በሽታ ተፈውሻለሁ፡፡እኔን ያዳነ ያድናችሁ በማለት ሰኔ 10/2009ዓ.ም አውደ ምህረት ላይ ቆመውበብዙ ደስታ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡[/read]