መመገብና ውኃ መጠጣት እንኳን አትችልም ነበር

አቶ እንዳወቅ አታሎ እባላለሁ፡፡ የመጣሁት ከባሕር ዳር ከተማ ከቀበሌ 07 ሲሆን ልጄ ትሕትና እንዳወቅ ትባላለች፤ በድንገት ታማ ሰውነቷ በሙሉ ሽባ ሆኖ መንቀሳቀስ እና መውጣት መግባት ይቅርና ምግብ መመገብና ውኃ መጠጣት እንኳን አትችልም ነበር፡፡ እኔም ተአምረኛነቱን ስለማውቅ ወደ ወንቅ እሸት ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም ይዣት መጣሁ፡፡ በወንቅ እሸት ገዳም ለሁለት ሳምንት በማስጠመቅ ብቻ ልጄ ዳነችልኝ፡፡ አሁን እንደ ማኛውም ሰው እየወጣች እየወረደች ጤነኛ ሆና ትገኛለች፡፡ ልጄን ለፈወሰልኝ ለአምላከ ቅዱስ ገብርኤል ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይግባው፡፡

የጨለመውን ተስፋችን አለመለመልን

     አቶ አብርሃም ሲሳይ እባላለሁ፤ ከባለቤቴ ከወይዘሮ ወርቄ ደስታው ጋር የመጣነው ከአዲስ አበባ ከተማ ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አካባቢ ከወረዳ አንድ ሲሆን ለአስር ዓመታት ተጋብተን በትዳር ስንኖር ልጅ አጥተን ልጅ ባየን ቁጥር [read more] እየሳሳን በኀዘን እንኖር ነበር፡፡ እግዚአብሔር ልጅ እንዲሰጠን እየለመንንና እየተሳልንም ከአስር በላይ በሚሆኑ ገዳማትና የጸበል ቦታዎች በመዞር ተማጽነን ነበር፡፡ ይሁን እንጅ ልጅ ልናገኝ ስላልቻልን ከእንግዲህ መቼም ቢሆን ልጅ የማግኘት ተስፋ የለንም ብለን ተስፋ ቆርጠን ተቀመጥን፡፡ አምና በ2009 ዓ.ም ባለቤቴ ወርቄ ደስታው የወንቅ እሸት ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳምንና የአባታችን የአባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያምን ዝና ሰምታ ብትነግረኝም እኔ ብዙ ቦታዎች ተመላልሼ ተስፋ ቆርጬ ስለነበር ወደ ወንቅ እሸት ለመምጣት ፈቃደኛ አልሆንኩም፡፡ ባለቤቴ ግን ብቻዋን መጥታ ጸበሉን ተጠምቃና ተስላ ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ በሚገርምና በሚደንቅ ቃል ኪዳኑ እግዚአብሔር ልመናዋን ሰምቶ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወንድ ልጅ ወልደን ይኼው ዛሬ ልጃችን ታቅፈን ተአምሩን ለመመስከር ነው የመጣነው፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ልጆች በምህረቱ የጎበኘበት ልዩ ገዳም የወንቅ እሸቱ ቅዱስ ገብርኤል የተሟጠጠውንና የጨለመውን ተስፋችን አለመለመልን፡፡ እኛን የሰማ ሁላችሁንም ይስማችሁ፡፡ [/read]

ልጅ መውለድ ባለመቻሏ እያዘነች ትኖር ነበር

ወይዘሮ አልማዝ አንባው ትባላለች፡፡ የመጣችው ከእስቴ ከቀበሌ 02 ሲሆን በአድያመ ዮርዳኖስ ወንቅ እሸት ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም የተደረገላትን ተአምር እንዲህ ስትል መስክራለች፡፡

በኩላሊት ጠጠር በሽታ ከአራት ዓመታት በላይ በሽተኛ ነበርኩኝ፡፡ ከዓመታት በፊት የአድያመ ዮርዳኖስ ወንቅ እሸት ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳምን ተአምራትና [read more] አባታችን አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ጌታ ድንቅ ጸጋ የሰጣቸው አባት መሆናቸውን ሰምቼ መጥቼ በዚህ ገዳም ተጠምቄ ከኩላሊት ጠጠር በሽታ ድኛለሁ፤ ተፈውሻለሁ፡፡ ከተፈወስኩ አሁን 14ኛ ዓመቴ ነው፤ ጤነኛ ሆኘ ሥራየን እየሠራሁ እገኛለሁ፡፡ በተጨማሪም ጎረቤቴ ሀብታም ይግዛው ትባላለች፡፡ ለብዙ ዓመታት ትዳር ይዛ ስትኖር መካን ሆና ልጅ አጥታ ስታዝን ትኖር ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ሰዎች ‹‹ይህች እንደ በቅሎ የማትወልድ›› በማለት ይሰድቧትና ይሳለቁባት ነበር፡፡ ባሏም ልጅ ካልወለድሽ አብረን ልንኖር አንችልም ብሎ ፈታት ተለያዩ፡፡ ሌላ ባል ብታገባም አሁንም ልጅ መውለድ ባለመቻሏ እያዘነች ስትኖር አምና ወደ ወንቅ እሸት ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም መጥታ ልጅ እንዲሰጣት ተስላ ሄደች፡፡ ዘንድሮ ወንድ ልጅ ወልዳ እንደ እናቶች ታቅፋ ስድቤን ያስወገደልኝ አምላከ አባ ዮሐንስ ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰገነ ይሁን እያለች ልዑል እግዚብሔርን እያመሰገነች፣ የአባታችን የአባ ዮሐንስን እድሜ ያርዝምልኝ እያለች በደስታ እየኖረች ነው፡፡ ለእኛ የደረሰ የወንቅ እሸቱ ቅዱስ ገብርኤል ይድረስላችሁ፡፡ [/read]

የማያቸው ልክ በሥጋ እንደ ማያቸው ሆነው ነበር

መምህር ንዋይ አቢዩ ይባላል፤ በአድያመ ዮርዳኖስ ወንቅ እሸት ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም የተደረገለትን ግሩም ተአምር እንዲህ ሲል መስክሯል፡፡ እኔ የመጣሁት ከአዴት ወረዳ ከቀበሌ 03 ሲሆን በመምህርነት እየሠራሁ እየኖርኩ እያለሁ የእራሴን ማንነት ለማወቅ ወደ ሆስፒታል በመሄድ ስመረመር በተደጋጋሚ የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽተኛ ነህ የሚል የሞት ዜና ተነገረኝ፡፡ እኔም ለሁለት ዓመታት ተስፋ ቆርጬ በኀዘን ከኖርኩ በኋላ [read more] በወንቅ እሸት ገዳም ሕመምተኞች ሁሉ ከማንኛውም በሽታ እንደሚፈወሱ ሰምቼ መጥቼ ስጠመቅ ሰንብቼ ሄድኩኝ ነገር ግን ብመረመርስ አለብህ ቢሉኝስ እያልኩ ፈራ ተባ እያልኩ ሳልመረመር ቀናት አለፉ:: እንዲህ ድኜ ይሁን አልዳንኩ ይሁን? በማለት እየተጠራጠርኩኝ በነበረበት ወቅት÷ አንድ ቀን እንደተኛሁ በሕልሜ ጸሐይ በነጭ ደመና ተከባ በሰረገላ ተጭና ወደ እኔ ትመጣለች፤ እኔም የማየው ሆኖ የማያውቅ ነገር አስደንግጦኝም አስገርሞኝም፣ ምንድነው እየሆነ ያለው ጸሐይ ወደ እኔ የምትሮጠው ለምንድነው እያልኩ ሳወጣ ሳወርድ ድንገት ከጸሐይዋ ውስጥ አባታችን አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ሰማያዊ ቀሚስ ለብሰው፣ በሰፊ የጠፍር መታጠቂያ ታጥቀው፣ መስቀልና ጭራቸውን ይዘው ይወጣሉ፤ እኔም ስለምወዳችው አባታችን አባ ዮሐንስ! አባታችን አባ ዮሐንስ እያልኩ ስደነቅ ከጸሐይዋ ሰረገላ ወርደው ወደ እኔ በመምጣት አይዞህ ልጄ አትጠራጠር ከበሽታህ ድነሃል ሂድና ተመርመር አትፍራ ብለው ባረኩኝ፡፡ የማያቸው ልክ በሥጋ እንደ ማያቸው ሆነው ነበር ከእንቅልፌ ስነቃ ግን ህልም ነበር፤ ያየሁት ነገር ሁሉ አስደነቀኝ፤ ተደሰትኩም፡፡ ወዲያው ተነስቼ በመጀመሪያ አዴት ጤና ጣቢያ ስመረመር ኤች አይ ቪ ኤድስ የለብህም ተባልኩ፤ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ባሕር ዳር በመሄድ የኤች አይ ቪ ኤድስ ታማሚዎች ሁሉ ክትትል ወደሚያደርጉበት ሀን ጤና ጣቢያ በመሄድ ስመረመር አሁንም ኤች አይ ቪ ቫይረስ በደምህ ውስጥ የለም የሚል አዲስ ዜና አዲስ የምስራች ሰማሁ ደስ ብሎኛል ደስ ይበላችሁ፡፡ በእውነት የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ እና ግሩም ነው የተደረገልኝን ለመናገር አንደበት ያጥረኛል እኚህን አባት የሰጠን የአባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም አምላክ ሕያው እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ [/read]

ከጭንቅላት ካንሰር ተፈወስኩኝ

ይስሃቅ ታደሰ እባላለሁ፡፡ እኔ የመጣሁት ከአዲስ አበባ ከወረዳ 11 ከቀበሌ 16/17 ሲሆን ለአምስት አመት ሙሉ በጭንቅላት ካንሰር በሽታ ስሰቃይ እኖር ነበር፡፡ በዚህ በሽታ ውስጥ ስኖር ቀን 7 ጊዜ ሌሊት ደግሞ 3 ጊዜ በአጠቃላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ10 ጊዜ በላይ ደም በአፍንጫዬ ይፈሰኝ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ሌሊት እንደተኛሁ ደም ቢፈሰኝና ወደ ጉረሮዬ ቢገባ ሊገለኝ ይችላል በማለት ለ5 ዓመት ሙሉ ሌሊት ተኝቸ አላውቅም ነበር፡፡ቀንም ቢሆን እየፈራሁ ከ3 ሰዓት የበለጠ ተኝቸ አላውቅም ነበር፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለህክምና ከ200 ሺህ ብር በላይ ጨርሸ [read more]ምንም መፍትሄ ባለማግኘቴ በመጨረሻ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄጄ እንድታከም እና ጭንቅላቴን ኦፕሬሽን እንድሆን ሪፈር ተባልኩ፡፡ እኔ ግን  ጭንቅላቴን መቀደድ አልፈልግም በማለት  ከዚህ በፊት በኢንተርኔት እግዚአብሔር በአባታችን በአባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ላይ አድሮ የሚሰራቸውን የማዳን ስራዎች እና በወንቅ እሸት ቅ/ገብርኤል ገዳም እስከ ኤች አይ ቪ ኤድስ ድረስ ከማንኛውም በሽታ ሰዎች ሲድኑ ስላየሁ ሰዎችን ከኤች አይ ቪ  ኤድስ የፈወሰ እግዚአብሔር እኔንም ይፈውሰኛል በማለት በ24 ሰአት ውስጥ ከ10 ጊዜ በላይ የሚፈሰኝን ደም ለመጥረግ በሻንጣየ ሶፍት ሞልቼ ይዤ ወደዚህ ገዳም ለመምጣት መንገድ ስጀምር አንደበቴ ተዘጋ ከዚያም ወደ ወንቅ እሸት ቅ/ገብርኤል ገዳም እንደገባሁ ከዚያችው ከገባሁባት ቀን ጀምሮ  ለ5 አመት ሙሉ ቀንና ሌሊት ሲፈሰኝ የነበረው ደም ቆመልኝ፡፡ ከደስታየ ብዛት የተነሳ ለሰዎች መዳኔን በምልክት ላስረዳ ብሞክርም መናገር ስለ ማልችል ሰዎች ሊረዱኝ አልቻሉም ነበር፡፡ በዚያች ዕለትም ለ5 አመት ሙሉ ተኝቼ የማላውቀው ሰው ሌሊቱን ሙሉ የሰላም ዕንቅልፍ ተኝቼ አደርኩ፡፡ ከዚያም በገዳሙ 5 ቀን ከቆየሁ በኋላ ድንገት ከልቤ ውስጥ አባ ዮሐንስ! የሚል ቃል ሲወጣ በጆሮየ ሰማሁት እኔም ምን ነገር ነው ብየ ስገረም ለ2ኛ ጊዜ አባ ዮሐንስ! የሚል ቃል ከልቤ ሲወጣ በትክክል በጆሮዬ ሰማሁት እኔም እንዴ ተናገርኩ እንዴ ብዬ ስደነቅ በ3ኛው አፌ ተከፍቶ አባ ዮሐንስ የሚል ቃል ከአፌ ወጣ አንደበቴም ተከፈተልኝ ዛሬ በእግዚአብሔር ቸርነት በአባታችን በአባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ጸሎት ተፈውሼ ደም አይፈሰኝ፤ እንቅልፌንም እንደልቤ ያለሃሳብ እየተኛሁ፤ ለ5 ቀናት ያህል ተዘግቶ የነበረው አንደበቴም ተከፍቶልኝ እጅግ ከባድ ከሆነው የጭንቅላት ካንሰር ተፈውሼ እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ በፊታችሁ ቆሜ እመሰክራለሁ፡፡ [/read]

ጸጉራቸው ከወገባቸው የደረሰ መነኩሴ መጥተው

ተማሪ ረድኤት ይልማ ትባላለች የመጣችው ከባህር ዳር ከተማ  ቀበሌ 11 ሲሆን በወንቅ እሸት ገዳም  የተደረገላትን ተአምር እንዲህ ስትል መስክራለች፡፡

በተደረገብን መተት ምክንያት እኔና እናቴ ሁለታችንም ጤናችን አጥተን እንኖር ነበር፡፡ እናቴ በህክምና የፊኛ ካንሰር ተብላ በተለያየ ህክምና እየለፋች እያለ በመጨረሻ ሞተች፡፡ እኔን ደግሞ [read more] ከጡቴ ስር እንደ ምላጭ ያለ ነገር ይቆርጠኛል፤ እንደ መርፌ ይወጋኛል፡፡ ያለ ማቋረጥ ደም ከአፍንጫየ ይነስረኛል፡፡ ወደ ሆስፒታል ስሄድ የቆሸሸ ደም ነው ይሉኛል፡፡ እንዲህ ሁኜ ስኖር በ2008 ዓ.ም ትምህርት ቤት ላይ ይጥለኝ ጀመር፡፡ ወደተለያዩ ጸበሎች ተዘዋውሬ መፍትሄ ሳጣ ወደ ወንቅ እሸት ገዳም መጣሁ፡፡ ወደ ገዳሙ መጥቼ ስጠመቅም  በአጠቃላይ  11 መርፌ፤ 4 የጃርት እሾህ፤ በፔስታል የታሰረ አፈር፤ ከሰል፤ 3 ድንጋይ፤  2 ምላጭ 3 እባብ ወጥቶልኝ ተፈውሻለሁ፡፡ ከዚህ ሌላም እህቴ ታማ  ለ3 ቀን ምግብ ሳትመገብ ከሰነበተች በኋላ በ3ኛው ቀን ሽታው የማያስቀርብ ነገር አስታወካትና ሞተች፡፡ ቤተ ሰብ ሁሉ ከቦ እያለቀሰ እያለ የወንቅ እሸት ተአምር ትዝ አለኝና የወንቅ እሸትን እምነት በጸበል በጥብጨ  ስረጫት ጸጉራቸው ከወገባቸው የደረሰ መነኩሴ መጥተው ተነሺ አሉኝ ብላ ብድግ ብላ ተነሳች፡፡ ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ የምንተክለው አትክልት ሁሉ እየደረቀ ጥቅም ሳይሰጥ ይቀር ነበር፡፡ እኔ ወንቅ እሸት ገዳም ከመጣሁ ወዲህ ግን አትክልቱ ለምልሞ አፍርቶ እየጠቀመን ይገኛል በማለት ምስክርነቷን ሰጥታለች፡፡ [/read]

ለ12 ዓመት ሙሉ መቆምም መቀመጥም አልችልም ነበር

ከታች የምትመለከቷት እህታችን ይለፉ ይታየው ትባላለች፡፡ የመጣችው ከጎንጅ ቆለላ ወረዳ ሲሆን በርዕሰ ባሕታውያን ሊቀ አዕላፍ ቆሞስ አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም የተደረገላትን ተአምር እንዲህ ስትል መስክራለች፡፡

እኔ ለ12 ዓመት ሙሉ መቆምም ሆነ መቀመጥ አልችልም ነበር:: እንደገናም በቀን ከአንድ ሙዝ እና ከአንድ ሻይ በቀር ምንም ዓይነት ምግብ አልበላም ነበር፡፡ በዚህ በሽታየ የተነሳ ቤተሰቦቼ እኔን በአልጋ እየተሸከሙ ያልወሰዱበት ጠንቋይና ደብተራ አልነበረም:: [read more] በተጨማሪም በተለያየ የጸበል ቦታ እያዞሩ ቢያስጠምቁኝም ምንም  ለውጥ አላገኘሁም፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ወደ ወንቅ እሸት ገዳም መጣሁ፤  በዚህ ገዳም ስኖር  ለነፍሳችን ያሉ ጸበልተኞች እያዘሉ ያስጠምቁኝ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አባታችን አባ ዮሐንስ   በመንፈስ ወደ እኔ መጥተው ‹‹ልጄ ዛሬ ጸበልተኛው ሲዘከር ለምን ከዝክሩ አልመጣሽም››? ይሉኛል፡፡ እኔም አባቴ እኔ እኮ እንጀራ አልበላም ምግቤ በቀን አንድ ሙዝ እና አንድ ሻይ ብቻ ነው ስላቸው በጣም ካዘኑ በኋላ ልጄ በይ እንግዲህ ጥሩ አድርጌ እሰራልሻለሁ ምግብ መብላት አለብሽ ይሉኛል፡፡ እሳቸው እንዲህ ካሉኝ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ  የእመቤታችን ጥር 21 የአስተርዕዮ ማርያም ክብረ በዓል ይሆንና ጓደኞቼ አዝለው ወደ ደብረ ዘይት አትሰድም ማርያም ወሰዱኝ፡፡ ከዚያም የቅዳሴው ስርዓት እንዳለቀ አባታችን አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም የባረኩትን የዝክር እንጀራ ጓደኞቼ አምጥተው ሰጡኝ እኔም በሁለት እጣቴ ስቀምሰው ሰውነቴ ሁሉ ተቃጠለ ከዚያ እንጀራውን መልሼ ሰጠኋቸው  ጩሂ! ጩሂ! ተነስተሸ ሩጪ! ሩጪ! የሚለኝ ነገር መጣ፤ በዚያን ጊዜም አዝለው የወሰዱኝ ጓደኞቼ እንደተቀመጡ ድንገት ተነስቸ መሮጥና እንደ እንቦሳ መዝለል ጀመርኩ፡፡ ለ12 ዓመት ሙሉ መቀመጥ የለ፤ መቆም የለ ከአልጋ ጋር ተጣብቄ የኖርኩት ሰው በዚያች  አባታችን አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም በባረኳት እና በሁለት ጣቴ ብቻ በቀመስኳት ቁራሽ እንጀራ ሙሉ በሙሉ ተፈውሼ ዛሬ ዘማሪ ሆኜ እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ እገኛለሁ በማለት በደስታ እየዘመረች  ምስክነቷን ተናግራለች፡፡[/read]

ጭንቅላቴ ወደ ግራም ሆነ ወደ ቀኝ አይዞርም ነበር

አስር አለቃ መንገሻ በይኖ ይባላሉ፡፡ የመጡት ከዳባት ወረዳ ወቅን ቀበሌ ሲሆን በዝነኛው ወንቅ እሸት ገብርኤል ገዳም የተደረገላቸውን ተአምር እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ እኔ ለ9 ዓመት ሙሉ በደም ግፊት በሽታ ታምሜ  ስሰቃይ እኖር ነበር፡፡ በመቀሌ መከላከያ ሆስፒታል እና በአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች ሆስፒታል  በተደጋጋሚ ተመርምሬ የዕድሜ  ልክ መድሃኒት እየወሰድክ ካልሆነ [read more]በቀር አትድንም ትሞታለህ ተብየ ነበር፡፡ ከህመሜም ጽናት የተነሳ በየቦታው ይጥለኝ ነበር፡፡ ጭንቅላቴ ገሮ አንገቴ ወደ ግራም ሆነ ወደ ቀኝ አይዞርም ነበር፡፡ በዚህ አስጨናቂ ህመም ውስጥ እያለሁ በህልሜ ወደ ወንቅ እሸት ገዳም እንድመጣ ስለታየኝ ወደዚህ ገዳም መጣሁ፡፡ መጥቸ ስጠመቅም ሰውነቴ ሁሉ ቀለለኝ ፤ኮፍያየን እንኳን መሸከም የማይችለው ጭንቅላቴ ዛሬ በርበሬ ተሸክሜ ከደ/ዘይት ማርያም እስከ ወንቅ እሸት ገዳም መውጣት መውረድ ቻልኩ፡፡ ወደ ጢስ አባይ ሄጄ ስመረመርም ምንም ዓይነት በሽታ የለብህም ተብያለሁ በማለት ሰኔ 14/2009ዓ.ም  የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ [/read]

ለ7 ዓመታት ከነበረብኝ የኤች አይ ቪ ኤድስ ነጻ

ወጣት ውዴ ዋለ ትባላለች፡፡ የመጣችው ከስማዳ ወረዳ ቀበሌ 15 ሲሆን ለ7 ዓመት ሙሉ የ H.I.V ኤድስ በሽታ ታማሚ ነበረች፡፡ ወደ ወንቅ እሸት ቅ/ገብርኤል ገዳም  መጥታ ሚያዚያ 8/2009 ዓ.ም ርዕሰ ባሕታውያን ሊቀ አዕላፍ ቆሞስ አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም  የትንሳኤን በአል ምክንያት በማድረግ ያዘጋጁትን እና ‹‹የሰው ልጆችን ከእስራታቸው  የሚፈታ አጋንንትን [read more] የሚያቃጥል ይሁንልን›› ብለው ባርከው ያቀረቡትን ዝክር ከተመገበች በኋላ ሚያዝያ 9/2009 ዓ.ም ወደ ጢስ አባይ ሂዳ ስትመረመር ለ7 ዓመት ሙሉ በደሟ ውስጥ ከነበረው አስከፊ የ H.I.V ቫይረስ በሽታ ነጻ ተብላ ምስክርነቷን በደስታ ተናግራለች፡፡ [/read]