ለ12 ዓመት ሙሉ መቆምም መቀመጥም አልችልም ነበር

ከታች የምትመለከቷት እህታችን ይለፉ ይታየው ትባላለች፡፡ የመጣችው ከጎንጅ ቆለላ ወረዳ ሲሆን በርዕሰ ባሕታውያን ሊቀ አዕላፍ ቆሞስ አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም የተደረገላትን ተአምር እንዲህ ስትል መስክራለች፡፡

እኔ ለ12 ዓመት ሙሉ መቆምም ሆነ መቀመጥ አልችልም ነበር:: እንደገናም በቀን ከአንድ ሙዝ እና ከአንድ ሻይ በቀር ምንም ዓይነት ምግብ አልበላም ነበር፡፡ በዚህ በሽታየ የተነሳ ቤተሰቦቼ እኔን በአልጋ እየተሸከሙ ያልወሰዱበት ጠንቋይና ደብተራ አልነበረም:: [read more] በተጨማሪም በተለያየ የጸበል ቦታ እያዞሩ ቢያስጠምቁኝም ምንም  ለውጥ አላገኘሁም፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ወደ ወንቅ እሸት ገዳም መጣሁ፤  በዚህ ገዳም ስኖር  ለነፍሳችን ያሉ ጸበልተኞች እያዘሉ ያስጠምቁኝ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አባታችን አባ ዮሐንስ   በመንፈስ ወደ እኔ መጥተው ‹‹ልጄ ዛሬ ጸበልተኛው ሲዘከር ለምን ከዝክሩ አልመጣሽም››? ይሉኛል፡፡ እኔም አባቴ እኔ እኮ እንጀራ አልበላም ምግቤ በቀን አንድ ሙዝ እና አንድ ሻይ ብቻ ነው ስላቸው በጣም ካዘኑ በኋላ ልጄ በይ እንግዲህ ጥሩ አድርጌ እሰራልሻለሁ ምግብ መብላት አለብሽ ይሉኛል፡፡ እሳቸው እንዲህ ካሉኝ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ  የእመቤታችን ጥር 21 የአስተርዕዮ ማርያም ክብረ በዓል ይሆንና ጓደኞቼ አዝለው ወደ ደብረ ዘይት አትሰድም ማርያም ወሰዱኝ፡፡ ከዚያም የቅዳሴው ስርዓት እንዳለቀ አባታችን አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም የባረኩትን የዝክር እንጀራ ጓደኞቼ አምጥተው ሰጡኝ እኔም በሁለት እጣቴ ስቀምሰው ሰውነቴ ሁሉ ተቃጠለ ከዚያ እንጀራውን መልሼ ሰጠኋቸው  ጩሂ! ጩሂ! ተነስተሸ ሩጪ! ሩጪ! የሚለኝ ነገር መጣ፤ በዚያን ጊዜም አዝለው የወሰዱኝ ጓደኞቼ እንደተቀመጡ ድንገት ተነስቸ መሮጥና እንደ እንቦሳ መዝለል ጀመርኩ፡፡ ለ12 ዓመት ሙሉ መቀመጥ የለ፤ መቆም የለ ከአልጋ ጋር ተጣብቄ የኖርኩት ሰው በዚያች  አባታችን አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም በባረኳት እና በሁለት ጣቴ ብቻ በቀመስኳት ቁራሽ እንጀራ ሙሉ በሙሉ ተፈውሼ ዛሬ ዘማሪ ሆኜ እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ እገኛለሁ በማለት በደስታ እየዘመረች  ምስክነቷን ተናግራለች፡፡[/read]

Leave a Reply