ልጅ መውለድ ባለመቻሏ እያዘነች ትኖር ነበር

ወይዘሮ አልማዝ አንባው ትባላለች፡፡ የመጣችው ከእስቴ ከቀበሌ 02 ሲሆን በአድያመ ዮርዳኖስ ወንቅ እሸት ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም የተደረገላትን ተአምር እንዲህ ስትል መስክራለች፡፡

በኩላሊት ጠጠር በሽታ ከአራት ዓመታት በላይ በሽተኛ ነበርኩኝ፡፡ ከዓመታት በፊት የአድያመ ዮርዳኖስ ወንቅ እሸት ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳምን ተአምራትና [read more] አባታችን አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ጌታ ድንቅ ጸጋ የሰጣቸው አባት መሆናቸውን ሰምቼ መጥቼ በዚህ ገዳም ተጠምቄ ከኩላሊት ጠጠር በሽታ ድኛለሁ፤ ተፈውሻለሁ፡፡ ከተፈወስኩ አሁን 14ኛ ዓመቴ ነው፤ ጤነኛ ሆኘ ሥራየን እየሠራሁ እገኛለሁ፡፡ በተጨማሪም ጎረቤቴ ሀብታም ይግዛው ትባላለች፡፡ ለብዙ ዓመታት ትዳር ይዛ ስትኖር መካን ሆና ልጅ አጥታ ስታዝን ትኖር ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ሰዎች ‹‹ይህች እንደ በቅሎ የማትወልድ›› በማለት ይሰድቧትና ይሳለቁባት ነበር፡፡ ባሏም ልጅ ካልወለድሽ አብረን ልንኖር አንችልም ብሎ ፈታት ተለያዩ፡፡ ሌላ ባል ብታገባም አሁንም ልጅ መውለድ ባለመቻሏ እያዘነች ስትኖር አምና ወደ ወንቅ እሸት ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም መጥታ ልጅ እንዲሰጣት ተስላ ሄደች፡፡ ዘንድሮ ወንድ ልጅ ወልዳ እንደ እናቶች ታቅፋ ስድቤን ያስወገደልኝ አምላከ አባ ዮሐንስ ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰገነ ይሁን እያለች ልዑል እግዚብሔርን እያመሰገነች፣ የአባታችን የአባ ዮሐንስን እድሜ ያርዝምልኝ እያለች በደስታ እየኖረች ነው፡፡ ለእኛ የደረሰ የወንቅ እሸቱ ቅዱስ ገብርኤል ይድረስላችሁ፡፡ [/read]

Leave a Reply