ጸጉራቸው ከወገባቸው የደረሰ መነኩሴ መጥተው

ተማሪ ረድኤት ይልማ ትባላለች የመጣችው ከባህር ዳር ከተማ  ቀበሌ 11 ሲሆን በወንቅ እሸት ገዳም  የተደረገላትን ተአምር እንዲህ ስትል መስክራለች፡፡

በተደረገብን መተት ምክንያት እኔና እናቴ ሁለታችንም ጤናችን አጥተን እንኖር ነበር፡፡ እናቴ በህክምና የፊኛ ካንሰር ተብላ በተለያየ ህክምና እየለፋች እያለ በመጨረሻ ሞተች፡፡ እኔን ደግሞ [read more] ከጡቴ ስር እንደ ምላጭ ያለ ነገር ይቆርጠኛል፤ እንደ መርፌ ይወጋኛል፡፡ ያለ ማቋረጥ ደም ከአፍንጫየ ይነስረኛል፡፡ ወደ ሆስፒታል ስሄድ የቆሸሸ ደም ነው ይሉኛል፡፡ እንዲህ ሁኜ ስኖር በ2008 ዓ.ም ትምህርት ቤት ላይ ይጥለኝ ጀመር፡፡ ወደተለያዩ ጸበሎች ተዘዋውሬ መፍትሄ ሳጣ ወደ ወንቅ እሸት ገዳም መጣሁ፡፡ ወደ ገዳሙ መጥቼ ስጠመቅም  በአጠቃላይ  11 መርፌ፤ 4 የጃርት እሾህ፤ በፔስታል የታሰረ አፈር፤ ከሰል፤ 3 ድንጋይ፤  2 ምላጭ 3 እባብ ወጥቶልኝ ተፈውሻለሁ፡፡ ከዚህ ሌላም እህቴ ታማ  ለ3 ቀን ምግብ ሳትመገብ ከሰነበተች በኋላ በ3ኛው ቀን ሽታው የማያስቀርብ ነገር አስታወካትና ሞተች፡፡ ቤተ ሰብ ሁሉ ከቦ እያለቀሰ እያለ የወንቅ እሸት ተአምር ትዝ አለኝና የወንቅ እሸትን እምነት በጸበል በጥብጨ  ስረጫት ጸጉራቸው ከወገባቸው የደረሰ መነኩሴ መጥተው ተነሺ አሉኝ ብላ ብድግ ብላ ተነሳች፡፡ ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ የምንተክለው አትክልት ሁሉ እየደረቀ ጥቅም ሳይሰጥ ይቀር ነበር፡፡ እኔ ወንቅ እሸት ገዳም ከመጣሁ ወዲህ ግን አትክልቱ ለምልሞ አፍርቶ እየጠቀመን ይገኛል በማለት ምስክርነቷን ሰጥታለች፡፡ [/read]

Leave a Reply