አቶ አብርሃም ሲሳይ እባላለሁ፤ ከባለቤቴ ከወይዘሮ ወርቄ ደስታው ጋር የመጣነው ከአዲስ አበባ ከተማ ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አካባቢ ከወረዳ አንድ ሲሆን ለአስር ዓመታት ተጋብተን በትዳር ስንኖር ልጅ አጥተን ልጅ ባየን ቁጥር [read more] እየሳሳን በኀዘን እንኖር ነበር፡፡ እግዚአብሔር ልጅ እንዲሰጠን እየለመንንና እየተሳልንም ከአስር በላይ በሚሆኑ ገዳማትና የጸበል ቦታዎች በመዞር ተማጽነን ነበር፡፡ ይሁን እንጅ ልጅ ልናገኝ ስላልቻልን ከእንግዲህ መቼም ቢሆን ልጅ የማግኘት ተስፋ የለንም ብለን ተስፋ ቆርጠን ተቀመጥን፡፡ አምና በ2009 ዓ.ም ባለቤቴ ወርቄ ደስታው የወንቅ እሸት ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳምንና የአባታችን የአባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያምን ዝና ሰምታ ብትነግረኝም እኔ ብዙ ቦታዎች ተመላልሼ ተስፋ ቆርጬ ስለነበር ወደ ወንቅ እሸት ለመምጣት ፈቃደኛ አልሆንኩም፡፡ ባለቤቴ ግን ብቻዋን መጥታ ጸበሉን ተጠምቃና ተስላ ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ በሚገርምና በሚደንቅ ቃል ኪዳኑ እግዚአብሔር ልመናዋን ሰምቶ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወንድ ልጅ ወልደን ይኼው ዛሬ ልጃችን ታቅፈን ተአምሩን ለመመስከር ነው የመጣነው፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ልጆች በምህረቱ የጎበኘበት ልዩ ገዳም የወንቅ እሸቱ ቅዱስ ገብርኤል የተሟጠጠውንና የጨለመውን ተስፋችን አለመለመልን፡፡ እኛን የሰማ ሁላችሁንም ይስማችሁ፡፡ [/read]