አስር አለቃ መንገሻ በይኖ ይባላሉ፡፡ የመጡት ከዳባት ወረዳ ወቅን ቀበሌ ሲሆን በዝነኛው ወንቅ እሸት ገብርኤል ገዳም የተደረገላቸውን ተአምር እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ እኔ ለ9 ዓመት ሙሉ በደም ግፊት በሽታ ታምሜ ስሰቃይ እኖር ነበር፡፡ በመቀሌ መከላከያ ሆስፒታል እና በአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች ሆስፒታል በተደጋጋሚ ተመርምሬ የዕድሜ ልክ መድሃኒት እየወሰድክ ካልሆነ [read more]በቀር አትድንም ትሞታለህ ተብየ ነበር፡፡ ከህመሜም ጽናት የተነሳ በየቦታው ይጥለኝ ነበር፡፡ ጭንቅላቴ ገሮ አንገቴ ወደ ግራም ሆነ ወደ ቀኝ አይዞርም ነበር፡፡ በዚህ አስጨናቂ ህመም ውስጥ እያለሁ በህልሜ ወደ ወንቅ እሸት ገዳም እንድመጣ ስለታየኝ ወደዚህ ገዳም መጣሁ፡፡ መጥቸ ስጠመቅም ሰውነቴ ሁሉ ቀለለኝ ፤ኮፍያየን እንኳን መሸከም የማይችለው ጭንቅላቴ ዛሬ በርበሬ ተሸክሜ ከደ/ዘይት ማርያም እስከ ወንቅ እሸት ገዳም መውጣት መውረድ ቻልኩ፡፡ ወደ ጢስ አባይ ሄጄ ስመረመርም ምንም ዓይነት በሽታ የለብህም ተብያለሁ በማለት ሰኔ 14/2009ዓ.ም የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ [/read]