ከጭንቅላት ካንሰር ተፈወስኩኝ

ይስሃቅ ታደሰ እባላለሁ፡፡ እኔ የመጣሁት ከአዲስ አበባ ከወረዳ 11 ከቀበሌ 16/17 ሲሆን ለአምስት አመት ሙሉ በጭንቅላት ካንሰር በሽታ ስሰቃይ እኖር ነበር፡፡ በዚህ በሽታ ውስጥ ስኖር ቀን 7 ጊዜ ሌሊት ደግሞ 3 ጊዜ በአጠቃላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ10 ጊዜ በላይ ደም በአፍንጫዬ ይፈሰኝ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ሌሊት እንደተኛሁ ደም ቢፈሰኝና ወደ ጉረሮዬ ቢገባ ሊገለኝ ይችላል በማለት ለ5 ዓመት ሙሉ ሌሊት ተኝቸ አላውቅም ነበር፡፡ቀንም ቢሆን እየፈራሁ ከ3 ሰዓት የበለጠ ተኝቸ አላውቅም ነበር፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለህክምና ከ200 ሺህ ብር በላይ ጨርሸ [read more]ምንም መፍትሄ ባለማግኘቴ በመጨረሻ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄጄ እንድታከም እና ጭንቅላቴን ኦፕሬሽን እንድሆን ሪፈር ተባልኩ፡፡ እኔ ግን  ጭንቅላቴን መቀደድ አልፈልግም በማለት  ከዚህ በፊት በኢንተርኔት እግዚአብሔር በአባታችን በአባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ላይ አድሮ የሚሰራቸውን የማዳን ስራዎች እና በወንቅ እሸት ቅ/ገብርኤል ገዳም እስከ ኤች አይ ቪ ኤድስ ድረስ ከማንኛውም በሽታ ሰዎች ሲድኑ ስላየሁ ሰዎችን ከኤች አይ ቪ  ኤድስ የፈወሰ እግዚአብሔር እኔንም ይፈውሰኛል በማለት በ24 ሰአት ውስጥ ከ10 ጊዜ በላይ የሚፈሰኝን ደም ለመጥረግ በሻንጣየ ሶፍት ሞልቼ ይዤ ወደዚህ ገዳም ለመምጣት መንገድ ስጀምር አንደበቴ ተዘጋ ከዚያም ወደ ወንቅ እሸት ቅ/ገብርኤል ገዳም እንደገባሁ ከዚያችው ከገባሁባት ቀን ጀምሮ  ለ5 አመት ሙሉ ቀንና ሌሊት ሲፈሰኝ የነበረው ደም ቆመልኝ፡፡ ከደስታየ ብዛት የተነሳ ለሰዎች መዳኔን በምልክት ላስረዳ ብሞክርም መናገር ስለ ማልችል ሰዎች ሊረዱኝ አልቻሉም ነበር፡፡ በዚያች ዕለትም ለ5 አመት ሙሉ ተኝቼ የማላውቀው ሰው ሌሊቱን ሙሉ የሰላም ዕንቅልፍ ተኝቼ አደርኩ፡፡ ከዚያም በገዳሙ 5 ቀን ከቆየሁ በኋላ ድንገት ከልቤ ውስጥ አባ ዮሐንስ! የሚል ቃል ሲወጣ በጆሮየ ሰማሁት እኔም ምን ነገር ነው ብየ ስገረም ለ2ኛ ጊዜ አባ ዮሐንስ! የሚል ቃል ከልቤ ሲወጣ በትክክል በጆሮዬ ሰማሁት እኔም እንዴ ተናገርኩ እንዴ ብዬ ስደነቅ በ3ኛው አፌ ተከፍቶ አባ ዮሐንስ የሚል ቃል ከአፌ ወጣ አንደበቴም ተከፈተልኝ ዛሬ በእግዚአብሔር ቸርነት በአባታችን በአባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ጸሎት ተፈውሼ ደም አይፈሰኝ፤ እንቅልፌንም እንደልቤ ያለሃሳብ እየተኛሁ፤ ለ5 ቀናት ያህል ተዘግቶ የነበረው አንደበቴም ተከፍቶልኝ እጅግ ከባድ ከሆነው የጭንቅላት ካንሰር ተፈውሼ እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ በፊታችሁ ቆሜ እመሰክራለሁ፡፡ [/read]

Leave a Reply